ETHIOPIAN ENTERPRISES DEVELOPMENT

Transforming manufacturing from trend to culture!

የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት አመራሮችና ሰራተኞች የ2016 በጀት አመት ዕቅድ አፈፃፀምን በመገምገም ላይ ናቸው፡፡

የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር አለባቸው ንጉሴ በግምገማ መድረኩ ላይ ባደረጉት የመክፈቻ ንግግር መድረኩ የተጠናቀቀውን በጀት አመት አፈፃፀም ገምግመን የተጀመሩ ውጤታማ ስራዎችን ለመጪው አመት በማሻገር የተሻለ አገልግሎት ለመስጠት በትጋትና በበለጠ ተነሳሽነት ስራችንን ለመቀጠል የምንመካከርበት ነው ብለዋል ፡፡

ዋና ዳይሬክተሩ በዚሁ መልዕክታቸው ስራችን ሰፊ፣ ሂደቱም አድካሚ ቢሆንም በበጀት አመቱ ከዕቅድ በላይ ያሳካናቸው ነገሮች እንዳሉ ሁሉ በተወሰነ መጠን የሚታዩ ክፍተቶች የታዩባቸውን አፈፃፀሞች በ2017 በትጋትና በተሻለ ተነሳሽነት ሁሉንም ባለድርሻ አካላት በማቀናጀት ማሳካት ይገባናል ብለዋል፡፡

የዘርፉ ሀገራዊ የትኩረት ማዕከል መሆን፣ ሐገራዊው የኢኮኖሚ ሪፎርም ማሻሻያና ተቋማዊ የሪፎርም ትግበራችን የፈጠረልንን ጠንካራ አደረጃጀትና ተቋማዊ አቅም በመጠቀም ዘርፉን በላቀ ደረጃ የማሳደግ እንቅስቃሴዎቻችን ግለታቸው ሳይበርድ ማስቀጠል ይገባናል ያሉት ዶ/ር አለባቸው ለዚህም መላው ሠራተኛ በተነሳሽነትና ሐገራዊ ሐላፊነት መንቀሳቀስ ይገባዋል ብለዋል።

News