ETHIOPIAN ENTERPRISES DEVELOPMENT

Transforming manufacturing from trend to culture!

የኢፌዴሪ ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ከአጠቃላይ ሰራተኞቹ ጋር የ2016 በጀት ዓመት የዕቅድ አፈፃፀምና የ2017 በጀት ዓመት ዕቅድ ውይይት ላይ የኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ አቶ መላኩ አለበል እንደተናገሩት እንደ ሀገር የተጀመሩ ሪፎርሞች ለአምራች ኢንዱስትሪ ዕድገት ሚናቸው የጎላ ነው ብለዎል።

በተለይ በቅርቡ የተደረገው የኢኮኖሚ ሪፍርም ለአምራች ኢንዱስትሪ የወጪ ኢንቨስትመንት ወደ ሀገር ውስጥ ለመሳብ፣ የወጪ ንግድና የማምረት አቅም አጠቃቀም ለማሳደግ ያለው ድርሻ ከፍተኛ ነው ብለዋል።

ባለፋት ዓመታት አምራች አንዱስትሪዎች የውጭ ምንዛሪ በቀላሉ የሚያገኙበት ዕድል ባለመኖሩ ምክንያት ግብዓት ለማሟላት የነበረውን ችግር ጭምር የሚያቃልል መሆኑን አስረድተዋል ።

እንደ ሚኒስትሩ ገለፃ የኢኮኖሚው ማሻሻያ ገቢ ምርትን የማያበረታታ በመሆኑ በውጪ ምርት ጥገኛ የሆነውን የሀገራችን ገበያ በሀገር ውስጥ ምርት ለመተካት ተዘጋጅቶ ወደ ስራ የገባውን የተኪ ምርት ስትራቴጂ ሙሉ በሙሉ ውጤታማ በሆነ መንገድ ለመተግበር ያግዛል ብለዋል።

News