በየተሰማሩበት የስራ ዘርፍ ለሀገር ኢኮኖሚያዊ እድገትና ሰላም መረጋገጥ የበኩላቸውን ድርሻ ላበረከቱ የአምራች ኢንዱስትሪ ኩባንያዎችና ተቋማት እውቅናና ሽልማት ተሰጠ
በተለያዩ የአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፎች በመሰማራት የሀገር ውስጥ ግብዓት በመጠቀም የእሴት ጭማሬ ምጣኔ፣ የተሰማሩበት የአምራች ኢንዱስትሪ ብዛት እና በሌሎች መመዘኛ መስፈርቶች ለሀገር ኢኮኖሚ ላቅ ያለ አበርክቶ ያላቸው 22 የአምራች ኢንዱስትሪ ኩባንያዎች በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ተመስገን ጥሩነህ እውቅናና ሽልማት ተበርክቶላቸዋል፡፡
በሀገር አቀፍ ደረጃ “የመሻገር ጥሪቶች የአዲስ ብርሃን ወረቶች ”በሚል መሪ በተከበረው ጳጉሜ 1 የመሻገር ቀን እውቅናና ሽልማት የተበረከተላቸው አምራች ኢንዱስትሪ ኩባንያዎች ለሌሎች የሀገራችን ባለሀብቶች ወደ አምራች ኢንዱስትሪ ዘርፉ በመቀላቀል የሀገራችንን የኢኮኖሚ መዋቅራዊ ለውጥ አሻጋሪ ተምሳሌቶች እንደሆኑ ከማሳወቅም ባለፈ እየሰሩ ያለው አኩሪ ስራ ለሀገርና ትውልድ አርዓያነት ያለው በመሆኑ ስራቸውን ከፍ ወዳለ ደረጃ እንዲያሳድጉ የቤት ስራ ለመስጠት ዓላማው ያደረገ መሆኑ ተገልጿል፡፡