የውይይቱ ዋና ዓላማ በቀጣይ ትኩረት በሚያስፈልጋቸው ጉዳዮች ላይ ያጠነጠ ሲሆን በዚህም ከሁለቱም ሃገራት የተውጣጡና አቅም ያላቸው የአምራች ኢንዱስትሪ ማህበረሰብ የልምድ ልውውጥ የሚያድረጉበት ስምምነት ላይ ተደርሷል።
በኢትዮጵያ እና በቻይና አቻ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች መካከል በተደረገው የሁለትዮሽ ውይይት ላይ የኢንዱስትሪ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ታረቀኝ ቡሉልታ ተገኝተዋል፡፡
በልምድ ልውውጡ የቻይና አምራች ባለሃብቶች ኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን የኢንቨስትመንት አቅም እና ክፍተት እንዲሁም ምቹ የፖሊሲና የኢንቨስትመንት ከባብያዊ ሁኔታ ተረድተው ኢንቨስት እንዲያደርጉ እንደሚረዳቸው ተገልጿል።
የኢትዮጵያ አምራች ባለሃብቶች በቻይና ያለውን እምቅ የኢንቨስትመንት አቅም ተረድተው ከቻይና ባለሃብቶች ጋር በጥምረት ኢንቨስት በማድረግ ትስስራቸውን እንዲያጠናክሩ እና አለም የደረሰበትን የኢንዱስትሪ አብዮት ልምድ በመቅሰም የኢንቨስትመንት ስራቸውን ለማሻሻል እንደሚያግዛቸው ተገልጿል።
በተጨማሪም በፎረሙ የተለያዩ የብሪክስን ትብብር የሚያጠናክሩ ተግባራት፡- የመስክ ጉብኝቶች ፣የብሪክስ አዲስ የኢንዱስትሪ አብዮት አጋሪነት ኤግዝብሽን፣ የቴክኒካል ጉዳዮች ልውውጥ የሚደረግባቸው የሰርዓት ፈጠራ መድረኮች፣ አባላቱ የሚደጋገፉበት ፕሮጀክቶችን የማፅደቅ እና የኢንዱስትሪ ፋይናንስ ድጋፍ ውይይቶች የተካሄዱ ሲሆን ይህም የኢንዱስትሪ ልማት ትብብር አገልግሎቱን የሚያጠናክሩ እና አባል ሃገራቱ የሚደጋገፉበትን የኢንዱስትሪ አቅም የሚፈጥር መሆኑን መረዳት ተችሏል።