ETHIOPIAN ENTERPRISES DEVELOPMENT

Transforming manufacturing from trend to culture!

የቼክ ሪፐብሊክ የአነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች ማህበርና የቼክ ኢንቨስት የልኡካን ቡድን በኢትዮጵያ በአነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዝ ልማት እየተከናወኑ በሚገኙ እንቅስቃሴዎችን አስመልክቶ ከተቋሙ አመራሮች ጋር ተወያዩ።

የልኡካን ቡድኑን የተቀበሉት የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር አለባቸው ንጉሴ እንደገለፁት በኢትዮጵያ ሠፊ የኢንዱስትሪ መሠረትን ለመጣል፣ የስራ ዕድል ለመፍጠርና ፍትሀዊ የሀብት ክፍፍልን ዕውን ለማድረግ የአምራች ኢንተርፕራይዝ ልማትን እንደዋንኛ ስልት በመውሠድ ሠፊ እንቅስቃሴ እየተደረገ ስለመሆኑ አብራርተዋል።

አምራች ኢንተርፕራይዞች ያሉባቸውን ውስብስብ ችግሮች በመቋቋም ዛሬም በውጤታማነት እየተጓዙ መሆኑን የገለፁት ዋና ዳይሬክተሩ በዚህም ሀገራዊውን የተኪ ምርት የማስፋትና የምርታማነት ንቅናቄ ትርጉም ባለው መልኩ ለመቀየር አስችሏል ብለዋል።

የልኡካን ቡድኑ ሠብሳቢ ሚስስ ክርስቲና ስትርናዶቫ በበኩላቸው ኢትዮጵያ ያሏትን ተፈጥሯዊ ፀጋዎች ታሳቢ አድርጋ በተለመችው የአምራች ኢንተርፕራይዝ ልማት ያገኘችው ስኬት አስደናቂ መሆኑን ገልፀው ይህንን ውጤታማነት ኢ ኮሜርስን በመሳሰሉ የቴክኖሎጂ አቅሞች ለመደገፍ ሀገራቸው መዘጋጀቷን ገልፀዋል።

የልኡካን ቡድኑ ከውይይትም ባሻገር በአምራች ኢንተርፕራይዞች የመስሪያ ቦታዎች በመንቀሳቀስ ጉብኝት አካሂዷል።

News