ETHIOPIAN ENTERPRISES DEVELOPMENT

Transforming manufacturing from trend to culture!

EED (መስከረም 09/01/2017ዓ.ም)

የተሞክሮ ልውውጡን የመሩት የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር አለባቸው ንጉሴ የአምራች ኢንተርፕራይዞች ዋነኛ ማነቆ የሆነውን የማምረቻና የመሸጫ ቦታ ችግር በክላስተር ኮርፖሬሽን ለመፍታት የድሬዳዋ አስተዳደር የአነስተኛና መካከለኛ ማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪዎች ክላስተር ኮርፖሬሽን አቋቁሞ እየሰራ መሆኑ ለሌሎችም ክልሎችም ተሞክሮ መሆን የሚችል እንደሆነ ተናግረዋል፡፡

አምራች ኢንተርፕራይዞች የክላስተር መሰረተ ልማት እንዲሟላላቸው ተቋሙ ከባለድረሻ አካላት ጋር በቅንጅት ይሰራል ያሉት ዋና ዳይሬክተሩ በድሬደዋ ከተማ አስተዳደር ስራውን በኮርፖሬሽን ደረጃ ለመምራት የታየውን ቁርጠኝነት ይበልጥ ለማጠናከር እንቅስቃሴ መኖሩ ለአምራቾች ትልቅ የምስራች እንደሆነ ገልፀዋል፡፡ ይህ ተቋም የተሠጡትን ተልዕኮዎች በተሟላ መልኩ መፈፀም እንዲቻለውም ተቋማቸው ሙሉ ድጋፉን እንዲሚያደርግ ገልፀዋል፡፡

ከድሬዳዋ አስተዳደር የአነስተኛና መካከለኛ ማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪዎች ክላስተር ኮርፖሬሽን የመጡ ተወካዩች በበኩላቸው ኮርፖሬሽኑ ከተቋቋመ 5 ዓመት መሆኑን በመግለጽ ሼድ በመገንባትና በማሰተዳደር ለአምራች ኢንተርፕራይዞች ድጋፍ እየሰጠ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

በኮርፖሬሽኑ የተሻለ ድጋፍና አገልግሎት መስጠት የሚያስችሉ አሰራሮችን ለመተግበርና ከባለድርሻ አካላት ጋር ተቀራርቦ ለመስራት የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት ድጋፍ እንደሚያስፈልገው ተወካዮቹ ጠይቀዋል፡፡

በኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት በኩል ተቋሙ በሚያከናውናቸው ተግባራትና ለዘርፉ ውጤታማነት በተዘጋጁ የድጋፍና የአሠራር ማዕቀፎች፣ መመሪያና ደንቦች እንዲሁም ተግባራዊ የክንውን ሒደቶችን አስመልክቶ ገለጻ የተደረገላቸው ሲሆን ከስራ ክፍሎች ጋር በቅርበት ተገናኝተው የአሠራር ሒደቶችን እንዲታዘቡም ሁኔታዎች ተመቻችቶላቸዋል፡፡

News