“በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ከ106 ሚሊየን ዶላር በላይ የማሽነሪ ሊዝና የስራ ማስኬጃ ብድርን በማመቻቸት 1ሺህ 565 ኢንተርፕራይዞችን ተጠቃሚ ማድረግ ተችሏል”

ወ/ሮ የመንዝወርቅ ግረፌ ፣ የአነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች ፋይናንስ ፕሮጀክት አስተባባሪ በኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት የአነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች ፋይናንስ ፕሮጀክት በ2016 በጀት ዓመት 1ሺህ 565 አነስተኛና መካከለኛ አምራች ኢንተርፕራይዞችን በሊዝ ፋይናንስና በስራ መስኬጃ ብድር ተጠቃሚ ማድረግ መቻሉን የፕሮጀክቱ አሰተባባሪ ወ/ሮ የመንዝወርቅ ግረፌ ተናገሩ። ከዓለም ባንክ በተገኘው የብድር ድጋፍ ከ106 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር በላይ ወጪ በማድረግ በኢትዮጵያ ልማት […]

በኢትዮጵያ እና በቻይና አቻ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች መካከል የሁለትዮሽ ውይይት ተካሄደ።

የውይይቱ ዋና ዓላማ በቀጣይ ትኩረት በሚያስፈልጋቸው ጉዳዮች ላይ ያጠነጠ ሲሆን በዚህም ከሁለቱም ሃገራት የተውጣጡና አቅም ያላቸው የአምራች ኢንዱስትሪ ማህበረሰብ የልምድ ልውውጥ የሚያድረጉበት ስምምነት ላይ ተደርሷል። በኢትዮጵያ እና በቻይና አቻ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች መካከል በተደረገው የሁለትዮሽ ውይይት ላይ የኢንዱስትሪ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ታረቀኝ ቡሉልታ ተገኝተዋል፡፡ በልምድ ልውውጡ የቻይና አምራች ባለሃብቶች ኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን የኢንቨስትመንት አቅም እና […]

የኢትዮጵያና ቻይና አምራች ኢንዱስትሪዎች ልምድ የሚለዋወጡበት መድረክ እዲዘጋጅ ስምምነት ላይ ተደረሰ

ከኢትዮጵያና ቻይና የተወጣጡና አቅም ያላቸው የአምራች ኢንዱስትሪ ማኅበረሰቦች ልምድ የሚለዋወጡበት መድረክ ለማዘጋጀት ስምምነት ላይ ተደረሰ፡፡ በኢትዮጵያና ቻይና የኢንዱስትሪ ሚኒስቴሮች መካከል የሀገራቱን ንግድና ኢንቨስትመንት ለማጠናከር ያለመ ምክክር ተደርጓል፡፡ በውይይቱ ላይም ከሁለቱ ሀገራት የተወጣጡና አቅም ያላቸው የአምራች ኢንዱስትሪ ማኅበረሰቦች የልምድ ልውውጥ የሚያድረጉበት መድረክ እዲዘጋጅ ስምምነት ላይ ተደርሷል። የልምድ ልውውጡ የቻይና አምራች ባለሃብቶች በኢትዮጵያ ያለውን የኢንቨስትመንት አቅም፣ ምቹ […]

“ኢትዮጵያ በአምራች ኢንተርፕራይዝ ልማት እያደረገችው ያለው እንቅስቃሴ አስደናቂ ነው” የቼክ ሪፐብሊክ የቢዝነስ ልኡካን ቡድን

የቼክ ሪፐብሊክ የአነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች ማህበርና የቼክ ኢንቨስት የልኡካን ቡድን በኢትዮጵያ በአነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዝ ልማት እየተከናወኑ በሚገኙ እንቅስቃሴዎችን አስመልክቶ ከተቋሙ አመራሮች ጋር ተወያዩ። የልኡካን ቡድኑን የተቀበሉት የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር አለባቸው ንጉሴ እንደገለፁት በኢትዮጵያ ሠፊ የኢንዱስትሪ መሠረትን ለመጣል፣ የስራ ዕድል ለመፍጠርና ፍትሀዊ የሀብት ክፍፍልን ዕውን ለማድረግ የአምራች ኢንተርፕራይዝ ልማትን እንደዋንኛ ስልት በመውሠድ ሠፊ […]

የድሬዳዋ አስተዳደር በ2016 በጀት ዓመት በግቦች አፈጻጸም በቢሮዎች መካከል ባካሄደው ውድድር የአስተዳደሩ የንግድ ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ አንደኛ በመዉጣት ተሸላሚ ሆኗል!

ቢሮው ለዚህ ስኬት የበቃው በተለይም ለአምራች ኢንዱስትሪ ልማትና ኢንቨስትመንት ባከናወናቸው ስራዎች እንደሆነ በመድረኩ ተገልጿል። የከተማ አስተዳደሩ ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ባዘጋጀው ሀገር አቀፍ የዕውቅና መድረክም ከክልልና ከተማ አስተዳደሮች መካከል አንደኛ በመውጣት ተሸላሚ መሆኑ አይዘነጋም። የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማትም በዚህ አጋጣሚ የቢሮዉን አመራሮችና መላዉ ሰራተኞች እንኳን ደስ አላችሁ ለማለት ይፈልጋል።

“እንደ ሀገር የተጀመሩ ሪፎርሞች ለአምራች ኢንዱስትሪ ዕድገት ሚናቸው የጎላ ነው” አቶ መላኩ አለበል

የኢፌዴሪ ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ከአጠቃላይ ሰራተኞቹ ጋር የ2016 በጀት ዓመት የዕቅድ አፈፃፀምና የ2017 በጀት ዓመት ዕቅድ ውይይት ላይ የኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ አቶ መላኩ አለበል እንደተናገሩት እንደ ሀገር የተጀመሩ ሪፎርሞች ለአምራች ኢንዱስትሪ ዕድገት ሚናቸው የጎላ ነው ብለዎል። በተለይ በቅርቡ የተደረገው የኢኮኖሚ ሪፍርም ለአምራች ኢንዱስትሪ የወጪ ኢንቨስትመንት ወደ ሀገር ውስጥ ለመሳብ፣ የወጪ ንግድና የማምረት አቅም አጠቃቀም ለማሳደግ ያለው ድርሻ […]

በ2016 በጀት አመት የአነስተኛና መካከለኛ አምራች ኢንተርፕራይዞችን የፋይናንስ አቅርቦት ችግር ለመቅረፍ ከ7.2 ቢሊዮን ብር በላይ ብድር ተሠራጭቷል፡፡

የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት በ2016 በጀት አመት ለ2,573 አምራች ኢንተርፕራይዞች ስራ ማስኬጃና የማምረቻ መሳሪያ አቅርቦት 7.27 ቢልዮን ብር እንዲቀርብ ማድረግ መቻሉን የተቋሙ የስራ አመራር ስራ አስኪያጅ አቶ ከላሊ ወ/ገብርኤል ገለፁ። የፋይናንስ አቅርቦት ስርጭቱ በ2.839 ቢልዮን ብር የ1,634 አነስተኛና መካከለኛ አምራች ኢንተርፕራይዞችን የስራ ማስኬጃ ብድር አቅርቦት ችግርን ለመፍታት ታቅዶ 83% ለሚሆኑት 1,352 አምራች ኢንተርፕራይዞች 2.999 ቢሊዮን ብር […]

ተቋሙ የ2016 በጀት አመት ዕቅድ አፈፃፀምን ገመገመ

የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት አመራሮችና ሰራተኞች የ2016 በጀት አመት ዕቅድ አፈፃፀምን በመገምገም ላይ ናቸው፡፡ የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር አለባቸው ንጉሴ በግምገማ መድረኩ ላይ ባደረጉት የመክፈቻ ንግግር መድረኩ የተጠናቀቀውን በጀት አመት አፈፃፀም ገምግመን የተጀመሩ ውጤታማ ስራዎችን ለመጪው አመት በማሻገር የተሻለ አገልግሎት ለመስጠት በትጋትና በበለጠ ተነሳሽነት ስራችንን ለመቀጠል የምንመካከርበት ነው ብለዋል ፡፡ ዋና ዳይሬክተሩ በዚሁ መልዕክታቸው ስራችን ሰፊ፣ […]

ለሀገር ኢኮኖሚ እድገትና ሰላም መረጋገጥ የበኩላቸውን አዎንታዊ አስተዋፅኦ ላበረከቱ አካላት እውቅናና ሽልማት ተሰጠ

በየተሰማሩበት የስራ ዘርፍ ለሀገር ኢኮኖሚያዊ እድገትና ሰላም መረጋገጥ የበኩላቸውን ድርሻ ላበረከቱ የአምራች ኢንዱስትሪ ኩባንያዎችና ተቋማት እውቅናና ሽልማት ተሰጠ በተለያዩ የአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፎች በመሰማራት የሀገር ውስጥ ግብዓት በመጠቀም የእሴት ጭማሬ ምጣኔ፣ የተሰማሩበት የአምራች ኢንዱስትሪ ብዛት እና በሌሎች መመዘኛ መስፈርቶች ለሀገር ኢኮኖሚ ላቅ ያለ አበርክቶ ያላቸው 22 የአምራች ኢንዱስትሪ ኩባንያዎች በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ተመስገን ጥሩነህ እውቅናና […]