EED ነሃሴ 19/2016 ዓ.ም
የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ከክልልና፣ ከተማ አስተዳደር፣ ተጠሪ ተቋማትና ባለድርሻ አካላት ጋር የ2016 በጀት ዓመት እቅድ አፈጻጻምና የ2017 ዕቅድን እየገመገመ ነው።
በመድረኩ የተሳተፉት የዘርፉ አመራሮች እንደተናገሩት በተጠናቀቀው በጀት ዓመት በርካታ ስኬቶችን ማስመዝገብ እንደቻሉ ገልጸዋል።
ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር በኢንዱስትሪው ዘርፍ የሚስተዋሉ ችግሮችን በዘላቂነት ለመፍታት ፖሊሲዎችና ስትራቴጂዎችን በማዘጋጀትና የሚያደርጋቸውን ድጋፍና ክትትል በተጠናከረ መልኩ መቀጠል እንዳለባቸው ጠቁመዋል።
እንደ ሀገር የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄን አቅጣጫ በመቀበል በክልልና በከተማ አስተዳዳር በማከናወን ዘርፋን የማነቃቃት፣ የሚስተዋሉ ችግሮችን በመፋታትና የሀገር ውስጥ አምራቾች ምርቶቻቸውን እንዲያስተዋውቁ ከፋተኛ ሚና ነበረው ብለዋል።
የዘርፉ አመራሮች አክለውም የሚስተዋሉ የመሰረተ ልማት በተለይም የኤሌትሪክ፣ የብድር አቅርቦት፣ የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሸን አገልግሎት የሚሰጡ ባለሙያዎች የክህሎት ክፍተቶችን እንደችግር አንስተዋል።
የአምራች ዘርፉ ይበልጥ ውጤታማ ለማድረግ ከቴክኒክና ሙያ እና ከከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ጋር በቅንጅት መስራት እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል።