የአነስተኛ እና መካከለኛ ኢንተርፕራይዝ ፋይናንስ ፕሮጀክት (SMEFP) አጠቃላይ እይታ
አነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዝ የፋይናንስ ፕሮጀክት በኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት አስተባባሪነት የተጀመረው አነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዝ የፋይናንስ ፕሮጀክት በተለይ በማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ ያለውን የፋይናንስ ክፍተት ለመፍታት ነው። ፕሮጀክቱ የተሰራው በ2014 በተደረገ ጥናት አነስተኛና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ከጥቃቅንና ትላልቅ ኢንተርፕራይዞች የበለጠ የብድር ጫና ያለባቸው መሆናቸውን በመለየት ነው። ከዓለም ባንክ እና ከአውሮፓ ኢንቨስትመንት ባንክ ጋር በመተባበር SMEFP የካፒታል እቃዎች ሊዝ ፋይናንስ፣ የስራ ካፒታል ብድር እና የንግድ ልማት አገልግሎቶችን ይሰጣል። ፕሮጀክቱ በኢትዮጵያ አነስተኛና አነስተኛ የፋይናንስ አቅርቦትን ለማሳደግ፣ኢንዱስትሪላይዜሽንን ለማስተዋወቅ እና የስራ እድልን ለማሳደግ ያለመ ነው።
ይህ የፕሮጀክት አካል /Component/ በኢትዮጵያ ልማት ባንክ በኩል የሚተገበር ሆኖ በዋና /Parent/ ፕሮጀክቱ 269 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር በጀት የተያዘለት ሲሆን በተጨማሪ ፋይናንሱ 180 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ተመድቦለታል፡፡ ይህ ገንዘብ ቀጥሎ በተገለጹት በሁለት መስኮት ለአነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች የሚቀርብ ይሆናል፡፡
ሀ) በቀጥታ በኢትዮጵያ ልማት ባንክ በኩል ብቁ ለሆኑ አነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች የሚቀርብ የካፒታል ዕቃዎች የሊዝ ፋይናንስ፣
ለ) የኢትዮጵያ ልማት ባንክ በንግድ ባንኮችና በማይክሮ ፋይናንስ ተቋማት በኩል ብቁ ለሆኑ አነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች የሚያቀርበው የስራ ማስኬጃ ብድር ነው።
ይህ የፕሮጀክት አካል /Component/ የሚተገበረው በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክና በፕሮጀክት ማስተባበሪያ ጽ/ቤቱ ጥምረት ሲሆን ለዚህም 1.87 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር በጀት ተይዞለታል፡፡ በዚህ ስር የሚሰሩ ስራዎች “ማዕከላዊ የኤሌክትሮኒክስ ዋስትና መመዝገቢያ መሳሪያ የመግዛት፣ የኪሳራ ምርመራ ቅኝትና የአበዳሪ/ተበዳሪ ህጋዊ አሰራር መዘርጋት” /Centralized electronic collateral registry/ ናቸው፡፡ በተጨማሪ ፋይናንሱ ተንቀሳቃሽ ንብረትን መሰረት ያደረገ የብድር ዋስትናና መረጃ ስርዓትን ለመዘርጋትና ለማጠናከር /Development of Movable Asset Based Lending/ 3 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር ተመድቦለታል፡፡
ይህ የፕሮጀክት አካል የሚተገበረው በፕሮጀክት ማስተባበሪያ ጽ/ቤቱ ነው፡፡ በዋና ፕሮጀክቱ የተያዘለት በጀትም 2.26 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ሲሆን ከተጨማሪ ፋይናንሱ 15 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ተመድቦለታል፡፡ በዚህ የፕሮጀክት አካል /Component/ ለአነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች የአቅም ግንባታ ስልጠና የሚሰጥ ሲሆን ይህም የንድፈ ሃሳባዊ ክህሎት (Soft skill) እና የቴክኒክና ሙያ ክህሎት (Technical skill) ስልጠናን የሚያጠቃልል ሲሆን ፕሮጀክት ማስተባበሪያ ጽ/ቤቱ ከኢትዮጵያ ፖስታ አገልግሎት ጋር በጋራ የሚሰራውን የኢ-ኮሜርስ እና የገበያ መረጃ ማዕከል ምስረታንም ይጨምራል፡፡
የሚከናወነው በፕሮጀክት ማስተባበሪያ ጽ/ቤቱ አማካኝነት ነው፡፡ ለዚህ የፕሮጀክት አካል /Component/ በዋና ፕሮጀክቱ 2.86 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር የተበጀተለት ሲሆን ከተጨማሪ ፋይናንሱ 2 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ተይዞለታል፡፡
የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዞችን ተወዳዳሪነት ለማሳደግ ፣ ትርጉም ያለው የስራ እድል ለመፍጠር እና ለአገሪቱ አጠቃላይ የኢኮኖሚ ዕድገትና ልማት የበኩሉን አስተዋፅኦ ለማበርከት ያለመ ነው ።