ETHIOPIAN ENTERPRISES DEVELOPMENT

Transforming manufacturing from trend to culture!

የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት በ2016 በጀት አመት ለ2,573 አምራች ኢንተርፕራይዞች ስራ ማስኬጃና የማምረቻ መሳሪያ አቅርቦት 7.27 ቢልዮን ብር እንዲቀርብ ማድረግ መቻሉን የተቋሙ የስራ አመራር ስራ አስኪያጅ አቶ ከላሊ ወ/ገብርኤል ገለፁ።

የፋይናንስ አቅርቦት ስርጭቱ በ2.839 ቢልዮን ብር የ1,634 አነስተኛና መካከለኛ አምራች ኢንተርፕራይዞችን የስራ ማስኬጃ ብድር አቅርቦት ችግርን ለመፍታት ታቅዶ 83% ለሚሆኑት 1,352 አምራች ኢንተርፕራይዞች 2.999 ቢሊዮን ብር እንዲሰራጭ ማድረግ ተችሏል፡፡

እንደአቶ ከላሊ ገለፃ በ2016 በጀት አመት ለአነስተኛና መካከለኛ አምራች ኢንተርፕራይዞች የተመቻቸው የፋይናንስ አቅርቦት ከ2015 ዓ.ም አፈጻጸም ጋር ሲነፃፀር ከፍተኛ ዕድገት አሳይቷል፡፡

በ2015 የተሠጠው አጠቃላይ የብድር መጠን 5.5 ቢልየን ብር እንደነበር አስታውሰዋል።

በበጀት ዓመቱ 7,229 የደረጃ ሽግግር ያደረጉ ሲሆን ይህ አፈፃፀምም እስካሁን በዘርፉ ከታዩት ስኬቶች ከፍተኛው ነው።

News