አምራች ኢንተርፕራይዞችን ማጠናከር ለሀገራዊ ኢኮኖሚ ሽግግርና ማህበራዊ ብልፅግና !
ነባራዊ ሐገራዊና ዓለማቀፋዊ ሁኔታዎችን፣ ሐገራዊ የአካባቢ ፀጋንና የገበያ ክፍተትን መነሻ በማድረግ አዲስ ወደ ስራ መግባት የሚፈልጉ ዜጎች በአምራች ኢንተርፕራይዝ ዘርፍ ለመሠማራት የሚያስችላቸውን የዘርፍና የምርት አይነት፣ አስፈላጊ ካፒታል፣ የጥሬ ዕቃና የሽያጭ የዕሴት ሠንሠለትና የሚጠቀሙበት የማምረቻ መሳሪያ ዝርዝር መግለጫ (specifications) እና መሰል ይዘቶችን የያዙ ልዩ ልዩ መነሻ ሠነዶችን ያዘጋጃል፤ ያሠራጫል፡፡
በማኑፋክቸሪንግ መስኮች ባለሀብቶች በስፋት እንዲሳተፉ ማድረግ የሚያስችል የኢንቨስትመንት ፕሮፋይል እንዲዘጋጅ ያደርጋል፣ የአዋጭነት ጥናቶችን በማደራጀት መረጃዎቹን በሴክተሩ ለመሰማራት ፍላጎት ላላቸው ባለሀብቶች እንዲሰራጭ ያደርጋል
ነባራዊ ሐገራዊና ዓለማቀፋዊ ሁኔታዎችን፣ ሐገራዊ የአካባቢ ፀጋንና የገበያ ክፍተትን መነሻ በማድረግ በዘርፉ ለመሠማራትም ሆነ ቢዝነሳቸውን ለማስፋት ለሚፈልጉ ባለሐብቶች ጥናትም መሠረት ባደረገ አግባብ የአዋጭነት ጥናት ያዘጋጃል፤ ያሠራጫል፡፡
የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዞችን ተወዳዳሪነት ለማሳደግ ፣ ትርጉም ያለው የስራ እድል ለመፍጠር እና ለአገሪቱ አጠቃላይ የኢኮኖሚ ዕድገትና ልማት የበኩሉን አስተዋፅኦ ለማበርከት ያለመ ነው ።