ብሔራዊ SMME

አምራች ኢንተርፕራይዞችን ማጠናከር ለሀገራዊ ኢኮኖሚ ሽግግርና ማህበራዊ ብልፅግና !

አነስተኛ ማኑፋክቸሪንግ ኢንተርፕራይዝ ማለት ከ 11 (አስራ አንድ) እስከ 50 (ሃምሳ) ቋሚ ሰራተኞች የያዘ እና ከብር 600,001 (ስድስት መቶ ሺህ አንድ) እስከ ብር 10,000,000 (አስር ሚሊዮን) ጠቅላላ ሐብት ያለው ኢንተርፕራይዝ ነው፤ ሆኖም ግን በሰው ኃይልና በጠቅላላ ሐብት መካከል አሻሚ ሁኔታ ሲፈጠር ጠቅላላ ሐብት ገዥ መስፈርት ይሆናል:: በኢትዮጵያ ይህን መስፈርት የሚያሟሉ 8,574 አነስተኛ አምራች ኢንተርፕራይዞች በስራ ላይ ይገኛሉ፡፡

2017_EFY_Updated_National_
Small_Manufacturing_
Enterprises_10_18

መካከለኛ ማኑፋክቸሪንግ ኢንተርፕራይዝ ማለት ከ 51 (ሃምሳ አንድ) እስከ 100 (መቶ) ቋሚ ሰራተኞች የያዘ እና ከብር 10,000,001 (አስር ሚሊዮን አንድ) እስከ 90,000,000 (ዘጠና ሚሊዮን) ጠቅላላ ሐብት ያለው ኢንተርፕራይዝ ነው፤ ሆኖም ግን በሰው ኃይልና በጠቅላላ ሐብት መካከል አሻሚ ሁኔታ ሲፈጠር ጠቅላላ ሐብት ገዥ መስፈርት ይሆናል:: በኢትዮጵያ ይህን መስፈርት የሚያሟሉ 4,177 መካከለኛ አምራች ኢንተርፕራይዞች በስራ ላይ ይገኛሉ፡፡

2017_EFY_Updated_National_
Medium_Manufacturing_
Enterprises_10_18