ቴክኖሎጂ፣ ፈጠራና ምርታማነት

አምራች ኢንተርፕራይዞችን ማጠናከር ለሀገራዊ ኢኮኖሚ ሽግግርና ማህበራዊ ብልፅግና !

ኤሌክትሮፕሊንግ

ተቋሙ ባለው ዘመናዊ ዎርክሾፕ በብረታብረትና ኢንጂነሪንግ ዘርፍ የተሠማሩ አምራች ኢንተርፕራይዞች ያሉባቸውን የኤሌክትሮፕሌቲንግ አገልግሎት እጥረት ታሳቢ በማድረግ አገልግሎት ይሠጣል

መለዋወጫ እቃዎችን ማምረት

ተቋሙ ባለው ዘመናዊ ዎርክሾፕ ምርትና ምርታማነትን የሚያሳድጉ ችግር ፈቺ አዳዲስ የቴክኖሎጂ ሃሳቦችን በማፍለቅና በማዳበር ተግባራዊ ያደርጋል፤ ምርጥ ቴክኖሎጂዎችን በመቅዳትና በማሻሻል ለተቋማትና አምራች አንተርፕራይዞች ያስተላልፋል፤ አምራች ኢንተርፕራይዞች በምርት ሒደት የሚያጋጥሟቸውን የመለዋወጫ ፍላጎቶች በፋውንደሪ ቴክኖሎጂ በማምረት ያቀርባል፡፡

የፈጠራ ማዕከል

ተቋሙ ያለውን ወርክ ሾፕ፣ ዲጂታል ላይብረሪ፣ 3ዲ ፕሪንተርና የስልጠና ማዕከላትን በመጠቀምና ዓለማቀፍ ባለድርሻ አካላተርን በማስተባበር የፈጠራ ፍላጎትና ክህሎት ያላቸውን ወጣቶች አሠባስቦ በኢንተርፕርነርሽፕ፣ ቢዝነስ አስተዳደርና መሠል ሶፍት ስኪል ስልጠናዎች ያበቃል፤ ቴክኒካል ስልጠናና ድጋፍ በማድረግም የሙያና የራዕይ ባለቤት እንዲሆኑ ያስችላል፡፡

የምርት ናሙናዎችን ማምረት

አዋጭነትን መሰረት በማድረግ ገቢ ምርቶችን የሚተኩና ለውጭ ገበያ ሊቀርቡ የሚችሉ ምርቶች እንዲለዩ በማድረግ የአመራረት ሒደት እንዲዘጋጅላቸው ያደርጋል፣ ለምርቶቹም ናሙና (Prototype) እንዲመረትላቸው በማድረግም ወደአምራች ኢንተርፕራይዞች በልዩ ልዩ አማራጮች እንዲተላለፉ ያደርጋል፡፡