የአቅም ግንባታ ስራዎች

አምራች ኢንተርፕራይዞችን ማጠናከር ለሀገራዊ ኢኮኖሚ ሽግግርና ማህበራዊ ብልፅግና !

ስልጠናዎች

ባለድርሻ አካላትን በማስተባበርና በመቀናጀት ለአምራች ኢንተርፕራይዞች እንዲሁም ከፌዴራል እስከ ታችኛው የመንግስት አስተዳደር እርከን አምራች ኢንተርፕራይዞችን ለሚደግፉና ለሚያስተባብሩ ፈፃሚና አስፈጻሚ አካላት በዘርፉ ልማት ፖሊሲ፣ የድጋፍ ማዕቀፎችና መሠል አስቻይ ሁኔታዎችና በልዩ ልዩ ሙያ ነክ ጉዳዮች ዙርያ ያለባቸውን ክፍተት መሠረት ባደረገ አግባብ ስልጠና ይሰጣል፤ ወይም ስልጠናቀዎች እንዲሠጡ ምቹ ሁኔታን ይፈጥራል፡፡

ተሞክሮ ቅመራና ሽግግር

በምርትና ምርታማነት የተሻለ አፈጻፀም ካላቸው ኢንተርፕራይዞች፣ ሀገራት፣ ተቋማትና የአገልግሎት መስጫ ጣቢያዎች ምርጥ ተሞክሮ እንዲቀመርና ከሌሎች የሚመለከታቸው አካላት ጋር በመተባበር እንዲሰፋ ያደርጋል፤ ውጤታማነቱንም ያረጋግጣል፡፡

የንግድ ልማት አገልግሎት /BDS/

አምራች ኢንተርፕራይዞች በንገድና ፋይናንስ አስተዳደር በኩል ያሉባቸውን ክፍተቶች መነሻ በማድረግ ጠንካራ ተቋማዊ ቁመናን ለመገንባት የሚያስችሏቸውን ስልጠናዎች እንዲያገኙ ይደግፋል፤ ሒደቱ በተሟላ ሁኔታ እንዲፈፀምም የማማከር አገልግሎት በመስጠት አምራቾች ጠንካራና ዘመናዊ የቢዝነስ አስተዳደር እንዲፈጥሩና ቀጣይነት ዕድገት እንዲኖራቸው ይደግፋል፡፡