የኢንቨስትመንት ማስተዋወቂያ እና ማመቻቸት

አምራች ኢንተርፕራይዞችን ማጠናከር ለሀገራዊ ኢኮኖሚ ሽግግርና ማህበራዊ ብልፅግና !

የገበያ ትስስር

አምራች ኢንተርፕራይዞች በሐገር ውስጥና በዓለማቀፍ ገበያ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ገበያ የማፈላለግ፣ የግብይት ክህሎትን የማሳደግ፣ አስቻይ የህግና የቢዝነስ ከባቢን እና በዲጂታል ማርኬቲንግና በኢኮሜርስ ድረ-ገፆች/ፖርታሎች ተጠቅመው ግብይት እንዲያካሄዱ  ውጤታማ የገበያ ትስስር ስርአት እንዲኖር ያደርጋል፡፡

አምራቾች ጥሬ እቃዎችን ከሐገር ውስጥና ከውጪ አምራቾች ማግኘት እንዲችሉ የግብአት ትስስር ስርአት ይዘረጋል፡፡

በተጨማሪም …

አምራች ኢንተርፕራይዞች እርስ በእርሳቸው፤ ከከፍተኛ ኢንተርፕራይዞች፤ እና ከሌሎች ተቋማት እና ድርጅቶች ጋር ቀጣይነት ያለው የገበያ ትስስር እንዲፈጥሩ ምቹ ሁኔታዎችን ይፈጥራል፤

አምራች ኢንተርፕራይዞች ምርታቸውንና ድርጅታቸውን የሚያስተዋውቁበት ብራንድ እንዲያዘጋጁ ያደርጋል፤

ተኪ ምርቶችን የሚያመርቱ አምራች ኢንተርፕራይዞች ምርታቸውን ለአስመጪዎች ወይም ለአገር ውስጥ ገዢዎች ማቅረብ እንዲችሉ አስፈላጊውን ድጋፍ ያደርጋል፤

አምራች ኢንተርፕራይዞች የውጭ ገበያ ዕድሎችን እንዲጠቀሙ እርስ በእርሳቸው እንዲሁም ከከፍተኛ አምራች ኢንተርፕራይዞች እና ከላኪ ድርጅቶች ጋር ቀጣይነት ያለው የገበያ ትስስር እንዲፈጥሩ ያደርጋል፤

አምራች ኢንተርፕራይዞች በሐገር ውስጥና በዓለማቀፍ ገበያ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ገበያ የማፈላለግ፣ የግብይት ክህሎትን የማሳደግ፣ አስቻይ የህግና የቢዝነስ ከባቢን ራሳቸውን የሚያስተዋውቁባቸውን ሁነቶች የመፍጠርና በዲጂታል ግብይት ንቁ ተሳታፊ እንዲሆኑ የማስቻል ስራዎችን ይሠራል፡፡

የክላስተር ማዕከላትና የመሰረተልማት አቅርቦት

የልማት መስሪያ ቤቱ ለአምራች ኢንተርፕራይዞች አገልግሎት የሚውሉ የማምረቻ፣ የማሳያና የመሸጫ ማዕከላት ይገነባል፤ ያስተዳድራል፤ ለተጠቃሚዎችም ያስተላልፋል፡፡ ክልሎች እና ከተማ አስተዳደሮች ለሚገነቧቸውና ማሻሻያዎች ለሚያደርጉባቸው የማምረቻ ማዕከላት ተገቢውን የቴክኒክ ድጋፍ ያደርጋል፣

በተጨማሪም የምረቻ ማዕከላትና ተቋማት ተገቢው የመሰረተ-ልማት (የመንገድ፣ የኃይል፣ የውሃ፣ የቴሌኮምና እና ሌሎች) ፍላጎት እንዲሟላ ከባለድርሻ አካላት ጋር በመቀናጀት ድጋፍ ፍላጎትን ከመለየት እስከ አቅርቦት ድረስ ድጋፍ ያደርጋል፡፡

ኢንቨስትመንት ፕሮሞሽን

የአምራች ኢንተርፕራይዞችን ሀገራዊ አቅም ለማሳየት፣ ተሞክሮ ለማለዋወጥና የሽያጭ አቅማቸውን ለማበልጸግ የሚያስችሉ ዓለም አቀፍ፣ ሐገር አቀፍና ክልል አቀፍ ሁነቶችንና መድረኮችን ያመቻቻል

በሀገር አቀፍና ዓለም አቀፍ ኤግዚቢሽንና ባዛሮችን በማፈላለግ አምራች ኢንተርፕራይዞች እንዲሳተፉባቸው ድጋፍ ያደርጋል፡

አዲስ በሚቋቋሙና በነባር የምርት ማሣያና መሸጫ ኢምፖሪዬሞችና በልዩ ልዩ ዲጂታል ፕላት ፎርሞች የአምራች ኢንተርፕራይዞች ምርቶች እንዲተዋወቁ ያደረጋል፤ ክልሎች ዲጂታል የግብይት ፕላትፎርሞችና ኢምፖሪዬም እንዲያቋቁሙና የአጠቃቀም መመሪያ አዘጋጅተው ወደ ስራ እንዲገቡ ድጋፍ ያደርጋል፤

የአምራች ኢንተርፕራይዞች ምርቶች ተፈላጊነታቸው እንዲጨምር ከሚመለከተው አካል ጋር በመቀናጀት የምርት ናሙናዎችን ውጪ ሀገር ለሚገኙ የኢትዮጵያ ኤምባሲዎችና ቆንስላዎች እንዲደርስ በማድረግ እንዲሁም ድረ-ገጽ፣ ካታሎግ፣ መፅሔት፣ ብሮሸርና ሌሎች አመቺ ዘዴዎችን በመጠቀም ምርቶቻቸው እንዲተዋወቁላቸው ያደርጋል፤

በማኑፋክቸሪንግ ዘርፉ ለመሰማራት ለሚፈልጉ የሀገር ውስጥ ባለሃብቶች በዘርፉ ማነቆዎች እና መልካም አጋጣሚዎች ላይ ማዕከል ያደረጉ የምክክር መድረኮችና የፕሮዳክሽን ስራዎች እንዲዘጋጁ ያደርጋል፤ ያሠራጫል፡፡